Homeቪዲዮ"ባለስልጣንን ጨምሮ ከ 137 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት ገደልኩ" ፋኖ

“ባለስልጣንን ጨምሮ ከ 137 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት ገደልኩ” ፋኖ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና

“ባለስልጣንን ጨምሮ ከ 137 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት ገደልኩ” ፋኖ

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

1 COMMENT

  1. ዛሬም እንደ ትላንቱ ገደልን እንጂ ሞተብን የማንሰማበት የፓለቲካ ቱልቱላ! ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክር የቁም ሙት የበዛበት ምድር። ለማንና ለምን እንደሚተኩስ ሳይለይ ምድሪቱን የሚያራቁት የጅል ስብስብ ራሱንም ሃገርንም ቆሜለታለሁ ለሚለውም ህዝብ የማይረቡ የዘር ሰካራም ስብስቦች። በመግደል፤ በማፈናቀል፤ በውሸት ፕሮፓጋንዳ ጊዜአዊ የሆነ የኢንተርኔት የስንጠቃ ወሬ ያፈላል እንጂ ለህዝባችን የሚጠቅመው አንድም ነገር የለም። ትምህርት ተቋረጠ ብሎ የሚያለቅሰው እኛ ካልተማርን እናንተም አትማሩም በማለት ት/ቤቶችን ዘግቶ መምህራንን የሚያስፈራራው አልፎ ተርፎም የሚገድለው ቡድን ነው። ህዝባችን ተራበ በማለት ሰሚ ለሌለው የዓለም ህዝብ ልመና የሚያቀርበው አርሶ አደሩን እያፈናቀለና እየገደለ አልፎ ተርፎም የተከመረ የእህል ክምርን በእሳት እያጋዬ ያለው ቡድን ነው። እብዶች በሚራወጡባት የአፍሪቃ ምድር በተለይም በሃበሻው ሰፈር ሰው የዛሬን እንጂ ለነገ ስለማያስብ ነገር ሁሉ አስረሽ ምቺው ነው። ጊዜ የሰጣቸው የብልጽግና ባለስልጣናት በተለይም ኦሮሞዎች በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የሚፈጽሙት በደል ሰማይ ጠቀስ ነው። ለምሳሌ ያህል ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ። በአዲስ አበባ አንድ በጥሩ ሁኔታ የተሰራ ቤት ውስጥ ቤተሰቦች መኖር ከጀመሩ 35 ዓመት ሆኗቸዋል። በድንገት ሊፈርስ ስለሆነ ሌላ ቦታ እንስጣችሁ ይባልና በተሰጣቸው ቦታ ቤት ሰርተው መኖር ይጀምራሉ። ግን ድሮ የኖሩበት ቤት አልፈረሰም። በህዋላ ሲያጠያይቁ ጊዜ ያነሳው ኦሮሞ እየኖረበት እንደሆነ ተረድ። ሁለተኛውም ተመሳሳይ ነው። አሁን የኮሪደር ሥራ አብቅቷል የሚፈርስ የለም በተባለበት ወቅት ላይ አመት በዓልን ጠብቀው ግፍ የማይፈሩት የኦሮሞ ባለስልጣኖች 70 ዓመት ሙሉ ቤተሰብ የኖረበትን ቤት ልናፈርስ ነው በማለት ሰውን ሲያንገላቱና በሰው እንባ ቆመው ሲስቁ ማየት መፈጠርን ያስጠላል። እንግዲህ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምሥራቅ እሰከ ምዕራብ ህዝባችን በብሄርተኞች ሾተል እየደማ ይገኛል። መፍትሄው ግን የመሳሪያ አፈሙዝ አይደለም። ያን መንገድ አልፈንበታልና አይረባም። ለማንም አልጠቀመም። ወደፊትም አይጠቅምም!
    የሚያሳዝነው ከወያኔና ከሻቢያ ከኦነግ/ሸኔ ጋር ሆነን እንዋጋለን የሚሉን የአማራ ፋኖዎች ናቸው። ማን ሆነና ህዝቡን እንዲህ ያበራየው ከጅምሩ። አፍራሽን አፍራሽ እየተካው እየተንኮታኮትን ባለንበት በዚህ ዘመን ከእነዚህ አጥፊና አማራ ጠል ሃይሎች ጋር አብረን እንሰራለን መባሉ ከእውቀት የመነጨ ሳይሆን የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ከሚሉት የጅል ፈሊጥ ነው። ወያኔ/ሻቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ሸኔ ከሰው የወጣ የአረመኔዎች ስብስብ ነው። እንዴት ነው እነዚህ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ አንድነት የሚመቹት? ተልካሻው የሃበሻ ፓለቲካ ባህር ላይ እንደሚንሳፈፈ ታንኳ ያለልቡ እየተናወጠ አስብናል ከሚለው ሳይሆን ካልታሰበው የባህር ዳርቻ ላይ እየተተፋ ስንቶችን ማግዶ/ራሱን ለስደትና ለእርዛት እንደ ዳረገ ያለፈ ታሪካችን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። መገዳደል መሰልጠን አይደለም። የብልጽግና ወታደር ገደልን። መቼ ነው የኢትዮጵያ ወታደር የሃገሪቱ መከላከያ የሚሆነው? የንጉሱ ወታደር/የደርግ/የወያኔ አሁን ደግሞ የብልጽግና ስናሳዝን። የአረንቋ ፓለቲካ! እልፈተ ቢስ ፓለቲካ…. የአንኮላ ስብስብ። የሰው ልጅ መኖር መለካት ያለበት እድሜ ልኩን ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ባሩድ እያሸተተና እያሸተተ በመኖሩ አይደለም። ለህዝቦች እኩልነትና አንድነት ዘርና ቋንቋን፤ ሃይማኖትን ሳይለይ ፍትህ ላጡ በመቆም እንጂ። ይህም መሳሪያ በማንሳት የሚመጣ ነጻነት አይደለም። ነገሮችን በማርገብና ህዝቡ እርስ በራሱ እንዲመክር እድልና ጊዜን በማመቻቸት እንጂ! ስለዚህ ገደልን/ማረክን/በሰኔ 4 ኪሎ ልንገባ ነው ገለመሌ የሚለው ተልካሻ ፉከራ ሁሉ የሚያሳየው የእሳቱን መድመቅና እንደ እሳት ራት ለመማገድ በመንደርደር ላይ መሆናቸውን ብቻ ነው። ጦርነት ይቁም! ወያኔና ሻቢያ ለሃገር አንድነት አይጠቅሙም። ብልጽግናም ልብ ገዝቶ በየስርቻው ያጎራቸውን ሰዎች ይፍታ! በስልጣናቸውና በዘራቸው በሌላው ላይ ጊዜው የእኛ ነው እያሉ ጮቤ የሚረግጡትንም አደብ ያስገዛ! በመገዳደል ብልጽግናም ስልጣኑን አያስረዝምም/ተፋላሚዎችም 4 ኪሎ አይደርሱም። መጫረሱ ይቀጥላል እንጂ! ተነጋገሩ። ሌላው ሁሉ ውሃን እንደመዝገን ይቆጠራል። አይረባም!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News