Homeመጣጥፍፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ብዙም ያልተዘመረላቸው ኢትዮጵያዊ

ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ብዙም ያልተዘመረላቸው ኢትዮጵያዊ

Advertisement
World Wide Travel Group
ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ

አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም
ከምድረ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

ጥር 2018  ዓ.ም.

እንደ መግቢያ

ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ በየትኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንደተወለዱ አላውቅም፡፡በሰውነት ደረጃ ላይ የቆሙ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ግን አውቃለሁ፡፡እኔ እድሜ ልኬን የኖርኩት አዲስ አበባ ከተማ ሲሆን እርሳቸው ደግሞ የሚወዷትን ሀገር ኢትዮጵያን ለቀው ከሄዱ ግማሽ ምእት አመት አለፋቸው፡፡እርሳቸው ከኢትዮጵያ ወደ ነጭሌው ሀገር ሲሄዱ እኔ የአራት አመት ጨቅላ ልጅ ነበርኩ፡፡ ለማናቸውም ዘመኑ በዋጀው ቴክኖሎጂ የሚያቀርቡት ከማርና ወተት የሚጣፍጥ የግጥም ስራዎቻቸውን ስከታተል አመታቶች ተቆጥረዋል፡፡ በእውነቱ ለመናገር እዚህ ሀገር ቤት እኛ ተቀመጥን እርሳቸው ደግሞ ባህር ማዶ ሆነው ከዋናው ከኢትዮጵያዊ ትውፊት ሳይወጡ እንደ ጥንቱ እንደ ጠዋቱ የአባቶቻችን ወግ ያገር ቤት ወግ ተመስረተው የሚያቀርቧቸው ታሪካዊና አስተማሪ ግጥሞቻቸው ግዜ የማይክዳቸው፣ግዜ የማሽራቸው የጥበብ ስራዎች ናቸው፡፡ ጋሼ ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፣ሻምበል አፈወርቅ ዮሀንስ፣አበበ ወርቄ፣ሀይሉ ገብረዮሀንስ(ገሞራው)፣ይልማ ደሬሳ፣ዶከተር አዘዘ፣ፊርማዬ አለሙ፣አለምጸሐይወዳጆ፣ኮሎኔል ሰሃሌ ደጋጎ እና ሻምበል አየለ ማሞ፣እንዲሁም ይልማ ገብርአብ(በሙዚቃ ግጥም ስራዎቻቸው) ወዘተ ወዘተ በግጥም ስራዎቻቸው ዝንተ አለም እንደሚታወሱት ሁሉ ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ታሪክ ስፍራውን የሚነሳቸው አልመሰለኝም፡፡ኢትዮጵያ የሰው ምድረበዳ በሆነችበት በዚህ ክፉ ዘመን እንደ ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁን የመሰሉ ስመጥር ኢትዮጵያውያንን ጤና እንዲሰጣቸው ጸሎታችንን እናደርሳለን፡፡ለማንኛውም በተባበረችው አሜሪካ አንድ ታዋቂና ኢትዮጵያዊ አዋቂዎችንና ባለውለታዎችን እየፈለገ በየአመቱ የሚሸልም ድርጅት (ሲድ SEED ተብሎ የሚጠራ ይመስለኛል፡፡) ፕሮፌሰር አዱኛውን ሸልሟቸው ይሆን የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡ ካልሸለማቸው እስቲ ልእለ ስራዎቻቸውን ይፈትሽ፡፡ እንደ መግቢያ ይቺን ካልኩ፡፡አንድ በተባበረችው አሜሪካ የሚኖር ወዳጄ ስለ ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ዘመኑ በዋጀው ቴክኖሎጂ ያወጋኝን ወግ ወደ ጽሁፍ ቀይሬ እንደሚከተለው አቀናብሬዋለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ ኑሯቸውን በዚሁ በአሜሪካ ያደረጉት ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ልክ የዛሬ ስድስት ዓመት ( 12/29/2019 ) ከሚኖሩበት ናፓ ከተማ ወደ ሣክራሜንቶ ብቅ ብለው ከሣክቶ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላቶች ጋር በቁም ነገር የታጀቡ አገር በቀል ወጎቻቸውን በአብሲኒያ ሬስቶራንት ከእራቱ ግብዣ በኋላ እያወጉን ነበር ።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከሣክራሜንቶ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሠባ ማይልስ ርቀት ላይ የምትገኘው ናፓ ሸለቆ በወይን ተክል ምርትና በወይን መጠጥ ጠመቃ ትታወቃለች ።

ከአስተዳደጋቸው ጀምረው ዛሬ የደረሱበትን ፣ ተረቶቹ፣ ምሣሌዎቹ፣ ሥነ ቃሎቹ ፣ ፈሊጦች ፣ ሥነ ሥርዓቶቹን በወጉ እየደረደሩ ዓያሌ ጉዳዮችን እያነሱ እየጣሉ ዋሽንቱን ከመሰንቆውና ከክራሩ በነበሩን ሕዝባዊ ዜማዎች እያጀቡ ምሽቱን ሕይወት ዘርተውበት ነበር ።

ከዜማው የጌታ መሣይ ትዝ አለኝ አገሬም አልቀራቸው ።

የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ
የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ ።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ባለፈው የአለቃ ገብረሐናን ጉዳይ ማጋራቴን አስታውሳለሁ ።

ሌላውን የፕሮፌሰር አዱኛው ጨዋታና ቁም ነገር ባጭሩ ብላችሁስ ?
የኢትዮጵያዊያንን ተረቶች ፣ ሥነቃሎች ፣ ምሣሌዎችና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ልቅም አድርጎ ያጠና ፈረንጅ ነበር አሉ ።

በርካታዎቹ ዕውነትነት ያላቸውና ማኀበረሰቡ ራሱን መግለፅ የሚችል አቅም ያላቸው መሆኑን ጭምር በአድናቆት በሚገባ ቸረ አሉን ። 

ነገር ግን አለ ፈረንጁ ሕልማችሁ ከነፈቺዎቹ … ወዲያና ወዲህ ናቸው ።

- Advertisement -

ያው አይረቡም ነገር ነው ። 

ሕልሙም በቅዠት ትርጉሙም በውሸት የተሞሉ ናቸው ዓይነት ።

ለምሣሌ ፦

ሕልመኛው – ትልቅ ባሕር ውስጥ ስዋኝ አደርኩ ።
ሕልም ፈቺው / ፈቺዋ – ከተማ ልትገባ ነው ።

ሃምሣ ሎሚ ለሃምሣ ሰው ጌጡ
ለአንድ ሰው ግን ሸክሙን እንዲህ በምሣሌ ገለጧት ።

ወዲህ ወደ ሲያትል የሚባል ግዛት ወደ መቶ ሺ የሚጠጉ የፊሊፕንስ አገር ሰዎች አሉ ። ማኅበረሰቡ ተደራጅቶ ተሰባስቧል ። አዲስ ፊሊፒኖ ወደዛ ግዛት ተሰዶ በመጣ ቁጥር እያንዳንዱ የማኅበረሰቡ አባላት ፊሊፒኖ አንድ ዶላር አዋጥቶ እንኳን ደህና መጣህ ለአዲሱ እንግዳ መቋቋሚያ ይሰጣል አሉ ። አዲሱ ነዋሪ ኑሮው ዳገት ሳይሆንበት ፉት ይላታል ማለት ነው ።

ልብ በሉ !

ሰጪው ራሱንም በብዙ ሳይጎዳ ተጠቃሚው ግን ሊያገኝ የሚችለውን መደገፊያ መጠን አስሉት ። እንደው ለነገሩ ሩብ ሆነ ግማሽ ክፍል ነዋሪ እንኳን አንድ ዶላር ቢሰጥ ተቋቋሚው ምን ያህል እንደሚያገኙ በግምት አስሉት። ለዚህ ዓይነት ጉዳይ ያልታደልነው እኛስ ከዚህ ቁም ነገርና የድጋፍ አጋርነት የት ዳርቻ ላይ አለን ?

ከተመሠረተ ረዥም ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት …

የሚገርመው የኛው ማኅበረሰባችን አባል ለመሆን የራቅንና አባል የሆኑቱ ደግሞ ዓመታዊ የአባላነት መዋጮ እንኳን የሚልከው በስንት የደብዳቤ መልዕክት ጋጋታ ነው ።

መሰለቻቸት ። የተስፋ በር መዝጋት ። 
ጀርባ ሰጥተን የቀረን ። 
ለነገዎቹ ልጆች ማሰብ ያቃተን ።

ሸሽተን ሸሽተን የት እንደርስ ይሆን?
ሁላችንም ሸቃባ ተጠያቂዎች ነን ።
ዛሬማ ለመኖሩም እኔንጃ !
ነገር ነው አለ ጓደኛዬ ንጉሥ ።

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News