Homeዜናየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ80 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ80 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት አጸደቀ

Advertisement
World Wide Travel Group
ፋይል

ቦርከና ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅድን ለማገዝ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የቀረበውን የ80 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ምህረቱ ሻንቆ ለምክር ቤቱ እንዳብራሩት፤ ፋይናንሱ በቀጥታ ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት የሚፈስ ሲሆን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውንና የኢነርጂ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ይውላል።

ብድሩ በዓመት 1.1 በመቶ ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበትና የ5 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ15 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

የብድር ስምምነቱ ከሀገሪቱ የብድር ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ ከመሆኑም በላይ፣ መንግሥት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የገቢ አሰባሰብን ለማሳደግ ለጀመረው ጥረት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ተመልክቷል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ምክር ቤቱም ረቂቅ አዋጁን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 1414/2018 አጽድቆታል።

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በጋዜጣዊ መግለጫ አምድ ስር ለንባብ የሚበቁ ጽሁፎች የቦርከናን አቋም ያንጸባርቃሉ ማለት አይደለም፡፡


ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian NewsBorkena English

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ኤክስ ፡ @zborkena 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News