
ቦርከና ዜና
ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ታዋቂ አርቲስቶች ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ መዝረፋቸው በኦዲት ምርመራ መረጋገጡ ተረጋግጧል።
በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሙስና የፈጸሙ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ኅብረተሰቡን የዘረፉ አርቲስቶች 78 ቢሊዮን ብርና 134 ሚሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ ሕጋዊ የባንክ ምንዛሪ ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸው (ኅብረተሰቡን መዝረፋቸው) በኦዲት ምርመራ መረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያስታወቀው የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲያቀርብ ነው፡፡
ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር፣ ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ፣ ወንጀል ነክ የሆኑ ምርመራዎች ላይ የሙስና ምርመራ ወንጀሎች እንዴት እንደሚፈጽሙ ሲያብራሩ፣ ሙስና በባህሪው እጅግ ውስብስና ድርጊት ፈጻሚው በረቀቀ መልኩ የሚፈጽመው በመሆኑ፣ ይህንን በማስረጃ ማረጋገጥ በጣም አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡
የሙስና ወንጀል ፈጻሚው ከራስ አርቆ ውጭ አገሮች ድረስ ንብረት የሚያሸሽና የሚያከማች በመሆኑ፣ እነዚህን ማውጣት ከባድ በመሆኑ ልዩ ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር ትብብር ማድረግንና የኦዲት ውጤቶችን የሚጠይቅ ሥራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኦዲት ሥራ ከሌለ በሙስና የደሰረውን ጉዳት መለካት እንደማይቻል፣ ምንም እንኳን ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖርም፣ በሚፈለገው ደረጃ መርምሮ ውጤት ላይ ለመድረስ ከባድ መሆኑን ተናግዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English






