Homeዜና7 የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና 28 ተማሪዎች በደህንነት ሰዎች ግቢ...

7 የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና 28 ተማሪዎች በደህንነት ሰዎች ግቢ ተወሰዱ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና

በምርጫ ሰበብ ያለአግባብ የታፈኑ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 የተቋማችን ተማሪዎች በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የደህንነት ሰዎች በትናትናው ዕለት ከኮሌጁ ቅጽር ግቢ ተወስደዋል ሲል የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታውቋል።

የትምህርት ተቋማት ለማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማስፈፀሚያነት እንደማይውሉ እየታወቀ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ግቢ ተማሪዎችን፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች በግዳጅ ከ5-7 የሚደርስ የምርጫ ካርድ በተለያዩ ስሞች እንዲያወጡ በመገደዳቸው ይህ ተግባር እንዲቆም ሲጠይቅ መቆየቱን አስታውሷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 29/2018 ዓ.ም የብልጽግና ፓርቲ በደብረ ማርቆስ ከተማ በጠራው የምርጫ ቅስቀሳ አልተሳተፋችሁም፤ የምርጫ ካርድም አላወጣችሁም፤ የተባሉ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 ተማሪዎቻችን በደህንነት ሰዎች ታፍነዋል ብሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉ መምህራን እና ተማሪዎቻችን እንዲለቀቁ ጠይቋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን በበኩሉ፣ የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፌስቡክ ገፅ ከሚያዚያ 27/2018ዓ.ም ጀምሮ ከተቋሙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል ብሏል።

የፌስቡክ ገጹ አድሚን የነበረው የተቋሙ ዲን አቶ አስጨንቅ ካሳ በጠላት ታፍነው በመወሰዳቸው ፔጁን ጠላት ሀሰተኛ መረጃ እያስተላለፈበት ይገኛል ብሏል።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian NewsBorkena English

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News